ProZ.com translation contests »
32nd Translation Contest: "Movie night" » English to Amharic » Entry by Meseret Alemayehu


Source text in English

Translation by Meseret Alemayehu (#37111) — Winner

To say that I was compelled by Parasite from start to finish is an understatement; its filming style with tracking shots are enthralling. Having watched several Korean films during the London Korean Film Festival, I was familiar with the usual genres employed in such films but Parasite seemed to defy them all! Parasite is comedic, in a quirky way, it is also a thriller, straddles class divisions and also depicts a family tale amongst other genres and is therefore likely to appeal to all ages.

Parasite truly deserves to be watched in a cinema to appreciate its nuances and the stylish cinematography. As a summary, to avoid spoilers, Parasite tells the tale of the interaction between the Park family and the Kim’s, an unemployed family, whose contrasting worlds collide with long lasting consequences.

[...]Bong Joon-Ho manages to pique the audience’s interest with brightly lit shots coupled with the effective use of indoor space, and it is surprising to realise, after the film’s 2 hour 12 minute length, that most of the scenes occur within the Park family’s home. The mundane elements of domesticity are displayed with an intriguing perspective showcasing Bong Joon-Ho’s flair. It is a slow burner but you will revel in its beauty and ingenuity as Parasite convinces that it operates solely on one level but it is in fact multi-layered and depicts social realism with empathy and pathos.

The cast are beguiling to watch, every facial movement and action is accentuated, even the mere act of walking up or down stairs can convey hidden meaning, which the camera fragments. Levels of unease are also created by virtue of that effective use of space with unusual camera angles and dramatic weather conditions ratcheting up that sensation. There is a surreal nature to Parasite, which its score emphasises, and furthermore the film adopts elements of the absurd devised in such an ingenious way which is truly cinematic magic. Parasite’s apparent eeriness will certainly keep you riveted and would not feel alien to the Twilight Zone school of filmmaking.

The actors are very impressive and add breadth to their roles creating relatability whilst seeming effortlessly cool. When Ki-Woo and Ki-Jeong Kim were working within the Park family home as private tutors they certainly epitomised this level of nonchalant, understated authority creating an aura of mysticism with the unspoken, almost mythical, tutoring techniques employed. Quite simply, the actors Park So-Dam and Choi Woo-Sik, as Ki-Woo and Ki-Jeong, are compelling to watch in the different directions that Parasite follows and they carry these performances seamlessly thereby inviting the audience to be on their side.

[...]Parasite is a remarkable piece of extremely skilful filmmaking, it is simply a must see film, and so I am looking forward to re-watching the film on its UK general release date.
ፓራሳይት ከመነሻው አንስቶ እስከ መገባደጃው ድረስ ቀልቤን ስቧል ብዬ ብናገር ማቃለል ነው የሚሆንብኝ። ገጸ ባህሪያቱን ማዕከል የሚያደርጉት የቀረጻ ስልቶቹ አስደሳች ናቸው። በለንደን የኮሪያ ፊልም ፌስቲቫል ወቅት በርካታ የኮሪያ ፊልሞችን ስላየሁ ለእንደነዚህ ዓይነት ፊልሞች በተለምዶ ጥቅም ላይ የሚውሉት ዘውጎች ለእኔ አዲስ አይደሉም፤ ሆኖም ግን ፓራሳይት እነዚህን ሁሉ ፊልሞች የሚገዳደር ይመስላል! ፓራሳይት ባልተጠበቀ መልኩ አስቂኝ እና ልብ አንጠልጣይ የሆነ፣ የማኅበራዊ መደብ ልዩነቶችን የሚያንጸባርቅ፣ ከሌሎች ዘውጎችም ጋር በማዋሃድ የቤተሰብ ታሪክን የሚተርክ ፊልም በመሆኑ፣ በሁሉም የዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎችን መማረክ የሚችል ነው።

የፓራሳይትን ስውር ልዩነቶችን እና ውብ የሆኑትን የሲኒማቶግራፊ ስልቶች ከልብ ለማጣጣም እንዲቻል በሲኒማ ቤት ውስጥ መታየት የሚገባው ፊልም ነው። ፊልሙን ላላዩት ሰዎች ገጽታዎቹን አሳልፌ ባለመስጠት ለማጠቃለል ያህል፣ ፓራሳይት የፓርክ ቤተሰብ እና የሥራ አጦቹ የኪም ቤተሰብ ተቃራኒ የኑሮ ሁኔታዎች መጋጨት የሚያስከትለውን ዘላቂ መዘዝ በማሳየት የሁለቱን ቤተሰቦች መስተጋብር ይተርካል።

[...]ቦንግ ጁን-ሆ በብርሃን የተሞሉ ቀረጻዎችን ውጤታማ ከሆነ የቤት ውስጥ ቦታ አጠቃቀም ጋር በማጣመር የተመልካቹን ትኩረት መሳብ የቻለ ሲሆን፣ ፊልሙ 2 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ላይ እስከሚደርስ ድረስ አብዛኛዎቹ ትዕይንቶች የፓርክ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተካሄዱ መሆናቸውን መገንዘብ አግራሞት ይፈጥራል። ተራ የሆኑ የቤተሰብ ኑሮ ገጽታዎች የተገለጹባቸው መንገዶች፣ ትኩረት የሚስበውን የቦንግ ጁን-ሆንን አመለካከት ያሳያል። ፓራሳይት ዘገም እያለ የሚሄድ ቢሆንም፣ ፊልሙ አንድ ትርጉም ብቻ ያለው እንዲመስልዎት እያሳመንዎ በእውነቷው ግን ብዙ የትርጉም ጥልቀቶች ያለው እንዲሁም ማኅበራዊ እውነታዎችን በርህራሄ እና በሰሜታ የሚገልጽ እንደሆነ ሲረዱ በውበቱና በብልሃቱ ይደሰታሉ።

ተዋንያኑ ለዕይታ የሚያስደምሙ ናቸው፤ እያንዳንዱ የፊት እንቅስቃሴ እና ድርጊት ጎልቶ ይታያል፤ በደረጃ ላይ መውጣት እና መውረድን የመሰለ ተራ ድርጊትም እንኳን በካሜራው የሚነጣጠል ድብቅ ትርጉም ሊይዝ ይችላል። ያልተለመዱ የካሜራ አቅጣጫዎችን ከውጤታማ የቦታ አጠቃቀም ጋር በማቀናጀት የተለያየ ደረጃ ያለውን የመረበሽ ስሜት የሚፈጥር ሲሆን፣ አስገራሚ የአየር ሁኔታዎችም ይህንን ስሜት ያጎሉታል። ፓራሳይት በማጀቢያ ሙዚቃው አማካኝነት አጽንዖት የሚሰጠው ህልም የሚመስል አሠራር አለው፤ ከዚህም ባሻገር ፊልሙ ፈጽሞ የማይመስሉ ነገሮችን እጅግ ብልህ በሆነ መልኩ ማካተት መቻሉ በእውነቱ ምትሃታዊ በሆነ የፊልም አሠራር መሠራት ያሳያል። የፓራሳይት አስፈሪነት በእርግጠኝነት ትኩረትዎን መሳብ የሚችል ሲሆን፣ ከትዋይላይት ዞን የፊልም አሠራር ዘይቤም ብዙም አይለይም።

ተዋንያኑ በጣም አስደናቂ ናቸው፤ ለሚጫወቱት ገፀ ባህሪያት ጥልቀት በመጨመር ከገሀድ ሁኔታዎች ጋር ተዛማጅነትን መፍጠር እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት ያለምንም ጥረት ጥሩ ሰዎችን መምሰል ችለዋል። ኪ-ዉ እና ኪ-ጆንግ ኪም በፓርክ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የግል አስጠኚ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት፣ በዚህ ደረጃ ላለው ግድየለሽ እና ስውር ሥልጣን ተምሳሌት በመሆን፣ ጥቅም ላይ ባዋሉት በቃላት ለማይገለጽ እና አፈ ታሪክ ለመሆን ብዙም በማይቀረው የማስጠናት ቴክኒክ ሚስጥራዊነት የሚንፀባረቅበትን ስሜት ይፈጥራሉ። ፓራሳይት በሚከተላቸው የተለያዩ አቅጣጫዎች ውስጥ ተዋንያን ፓርክ ሶ-ዳም እና ቾይ ዉ-ሲክን እንደ ኪ-ዉ እና ኪ-ጆንግ መመልከት ቀልብ የሚስብ ሲሆን፣ እነኚህን ትወናዎች ያለምንም ጉድፈት በመጫወት ተመልካቹን ከእነሱ ጎን እንዲቆም ይጋብዛሉ።

[...]ፓራሳይት በከፍተኛ ጥበብ የተሞላ እና አስደናቂ የሆነ የፊልም ሥራ ነው፤ ነገሩን ለማሳጠር ፊልሙ መታየት ያለበት ፊልም ነው፤ ፊልሙ ዩ.ኬ ውስጥ ለዕይታ ሲቀርብ በድጋሚ ለማየትም በጉጉት እየጠበኩኝ ነው።


Discuss this entry